የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በባህርዳር ከተማ ሊካሄድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በደመቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ ተነገረ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ፣ የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የቴክኒክ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው በማቅናት አስፈላጊውን ዝግጅት እያከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቋል።

ይህ የውድድር መድረክ በዋናነት አዳዲስ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራትና የውድድር እድሎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

በዚሁ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ላይ የግል ተሳታፊዎችን ጨምሮ ከ6 የተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ 91 አትሌቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል። በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ለሚያጠናቅቁ አትሌቶችም የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።

ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ጊዜ አድነው እና አቶ መሐሪ ነጋሽ በጋራ የሰጡት ሲሆን፣ ውድድሩ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በቀጥታ ስርጭት ለተመልካች እንደሚተላለፍ ታውቋል።

#EthiopianAthletics #BahirDar #StreetRace #10KRun #EthiopianSport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: