የተከለከለ ንጥረ መድሃኒት በመጠቀሟ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለአራት ወራት ከውድድር ታገደች
የአትሌቲክስ ስነ ምግባር ክፍል (AIU) ባለ ሁለት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና እና የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ባለቤቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ላይ የ4 ወራት እገዳ መጣሉን ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ አደረገ።
ይህ እገዳ እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
የእገዳው መንስኤ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ከተወሰደባት የሽንት ናሙና ላይ ‘ሌትሮዞል’ የተባለ የተከለከለ ንጥረ ነገር በመገኘቱ ነው።
አትሌቷ ክሱ በደረሳት ማግስት ንጥረ ነገሩ ለታመመችው ህክምና በሀኪም የታዘዘላት መሆኑን የሚያሳይ ሙሉ የህክምና ሰነድ አቅርባለች።
የዓለም አትሌቲክስ የህክምና ኮሚቴ ጉዳፍ ህክምናው እንደሚያስፈልጋት ቢያረጋግጥም፣ ከዓለም ፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) አስቀድማ የህክምና ፈቃድ (TUE) ሳታስፈቅድ በመቅረቷ የላቀ ኃላፊነት ህግን ተላልፋለች ብሏል።
ይሁን እንጂ አትሌቷ ሆን ብላ ያደረገችው አለመሆኑ በመረጋገጡ እና ጥፋቱን በፍጥነት በመቀበሏ፣ ሊጣልባት ይችል የነበረው የሁለት ዓመት ቅጣት ወደ አራት ወራት ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.