የወልድያ ከተማ ለዶ/ር አረጋ ይርዳው የክብር ሐውልት አቆመ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የወልድያ ከተማ አስተዳደር ለከተማዋ እድገት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ዶ/ር አረጋ ይርዳውን የክብር እውቅና ሰጥቷል። የዚሁ እውቅና አካል የሆነውና በከተማዋ አዳጎ አደባባይ የተገነባው የክብር ሐውልት ተመርቆ ለህዝብ እይታ በቅቷል።

​የከተማ አስተዳደሩ ይህንን የክብር ሐውልት ያቆመው ዶ/ር አረጋ ይርዳው በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በኢኮኖሚ ግንባታ ዘርፎች ላሳዩት አርአያነት ያለው አመራርና ለወልድያ ከተማ የልማት አሻራ ምልክት እንዲሆን ታስቦ መሆኑን ገልጿል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: