ደቡብ ኮሪያ ቼክ ሪፐብሊክን አሸነፈች
#Ethiopia | 23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር ዛሬ በይፋ ሲጀመር በመክፈቻው ጨዋታ ሜክሲኮን የገጠመችው ደቡብ አፍሪካ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች።
ለሜክሲኮ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ዩሊያን ኩዊኖኔስ በመጀመሪያው አጋማሽ በ9ኛው ደቂቃ ላይ እንዲሁም ራውል ሂሚኔዝ በ68ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል።
በርካታ ካርዶች በታዩበት በዚህ ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ 50ኛው ደቂቃ ላይ የደቡብ አፍሪካው ተከላካይ ስፊፎሌ ሲቶሌ በብሪያን ጉቴሬዝ ላይ በፈፀመው ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። መደበኛው የጨዋታ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሰባት ደቂቃ ሲቀረው ደግሞ ቴምባ ዝዋን ሁለተኛውን ቀይ ካርድ የተመለከተ ሲሆን ይህም በባፋና ባፋና የዓለም ዋንጫ ታሪክ አራተኛው ቀይ ካርድ ሆኖ ተመዝግቧል።
ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ሲቀረው በጭማሪ ሰዓት 92ኛው ደቂቃ ላይ የሜክሲኮው ሴዛር ሞንቴዝ የጨዋታውን ሦስተኛ ቀይ ካርድ አይቷል።
የታሪካዊው አዝቴክ ስታዲየም 21ኛ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የሆነውና የሁለቱ ሀገራት ሁለተኛ የጋራ ግንኙነት በሜክሲኮ አሸናፊነት ተጠናቋል።
ውድድሩን ከሚያዘጋጁት ሀገራት አንዷ የሆነችው ሜክሲኮም ምድብ አንድን በበላይነት መምራት ጀምራለች።
ደቡብ ኮሪያ ቼክ ሪፐብሊክን በመርታት የዓለም ዋንጫ ቆይታዋን በድል ጀምራለች።
በ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ አንድ መጀመሪያ ጨዋታ ደቡብ ኮሪያ ቼክ ሪፐብሊክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አመርቂ አጀማመር አድርጋለች።
ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ በተደረገው በዚህ ጨዋታ ሁዋንግ ኢን ቢዩም እና ኦ ሄዩን ጊዩ የደቡብ ኮሪያን ግቦች አስቆጥረዋል።
የቼክ ሪፐብሊክን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ደግሞ ከርጂች ነው።
ከ20 ዓመታት ረጅም እረፍት በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫው መድረክ የተመለሰችው ቼክ ሪፐብሊክ መጀመሪያ ግብ በማስቆጠር መምራት ብትችልም በመጨረሻ ግን ነጥብ አሳልፋ ለመስጠት ተገዳለች።
በአሁኑ ወቅት ምድብ አንድን አስተናጋጇ ሜክሲኮ እና ደቡብ ኮሪያ በእኩል ሦስት ነጥብ እየመሩ ይገኛሉ።
#WorldCup2026 #Football #Soccer #Mexico #SouthAfrica #SouthKorea #CzechRepublic #SportNews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.