አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ አጋርታለች።

ከእርሷ ጋር ተያይዞ ለቀረበው ዜና ምላሽ በሰጠችበት እንደገለጸችው የመውለድ አቅሟን ለማሻሻል በሃኪሟ ትዕዛዝ መሠረት የሌትሮዞል የተሰኘ ማሟያ መድኃኒት ስትወስድ ቆይታለች።

በአሁኑ ወቅት እርግዝናዋ በጥሩ ሁኔታና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የገለጸችው አትሌቷ ልጇ እንደተወለደች ወደምትወደው የስፖርት ውድድር በፍጥነት ለመመለስ ተስፋ እንደምታደርግ አስታውቃለች።

በተጨማሪም ለደጋፊዎቿ በሙሉ ላሳዩዋት ፍቅርና ድጋፍ ምስጋናዋን ያቀረበች ሲሆን የዓለም አትሌቲክስ ክፍል ላሳያት ግንዛቤና ድጋፍ አድናቆቷን ገልጻለች።

#gudaftsegay #athletics #ethiopianathletics #sportsnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1