ክብርት ዳኛዋን በችሎት የገደለው እራሱን አጠፋ።

- Advertisement -
Sidebar AD

በችሎት አዳራሽ በሽጉጥ ክብርት ዳኛዋን እና ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ ከ3ኛ ፎቅ ላይ እራሱን ወርውሮ ህይወቱን አጠፋ።

ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በሆለታ ወልመራ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በችሎት አዳራሽ የቤተሰብ ክርክርን መዝገብ ስትመለከት የነበረችው ክብርት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ እንዲሁም የክርክሩ አካል የሆነች የተከሳሹ የቀድሞ ባለቤት ወይዘሮ አልማዝ መኮንን በተከሳሹ በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸውን እንዲያልፍ ማድረጉ አይዘነጋም።

በዕለቱም እራሱ ላይ በመተኮስ ቆስሎ የነበረዉ አቅነዉ በቀለ የተባለው ግለሰብ በፖሊስ ጥበቃ እየተደረገ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ላይ ነበር።

ሆኖም ግለሰቡ በዛሬው ቀን ሕክምናውን ጨርሶ ከሆስፒታሉ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ጊዜ ላይ ከሆስፒታሉ ሕንፃ 3ኛው ፎቅ በመስኮት እራሱን በመወርወር እራሱን ማጥፋቱ ተረጋግጧል።

Via: ታሪክ አዱኛ


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2