ኢራን ከአሜሪካ ጋር የገባሁት ስምምነት አልተከበረም በሚል የሆርሙዝ ሰርጥን መልሳ መዝጋቷን አስታወቀች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢራን ማዕከላዊ ወታደራዊ ዕዝ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የምትፈጽመው ጥቃት ከአሜሪካ ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ በመሆኑ የሆርሙዝ ሰርጥን መዝጋቱን አስታውቋል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ባሕር ኃይል የባሕር መተላለፊው ለሁሉም መርከቦች በመዘጋቱ ማናቸውም መርከቦች የወደ ሰርጡ የሚቀርቡ ከሆነ ለአደጋ ስለሚጋለጡ መርከባቸውን ከሆርሙዝ እንዲያርቁ አስጠንቅቋል።

አብዮታዊ ዘቡ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ባቀረበው መግለጫ አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ አርብ ዕለት ሙሉ ለሙሉ ለመርከቦች የተከፈተው የባሕር መተላለፊያ ለሁሉም መርከቦች ተመልሶ ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል።

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በደረሰችው የመግባቢያ ስምምነት ላይ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታካሂደው ጥቃት እንደሚቆም የተገለጸ ቢሆንም አሁንም ጥቃቱ በመቀጠሉ ኢራን ስምምነቱ ተጥሷል ማለቷን የቢቢሲ እና አልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#Ethiopian Broadcasting Corporation #HormuzStrait #iran #USA #peace


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1