የያን ዲዮማንዴ ልብ ሰባሪ የህይወት ታሪክ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በስፔኑ ክለብ ሌጋኔስ የሚጫወተው የኮትዲቯር ተከላካይ ያን ዲዮማንዴ፣ በህይወቱ ላለፈችው እህቱ የጻፈው ልብ የሚነካ የትዝታ መልእክት የአለምን ትኩረት ስቧል።

​ያን ዲዮማንዴ በ”ዘ ፕሌየርስ ትሪቢዩን” መድረክ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ፣ እግር ኳስ ለመጫወት ያደረገውን እልህ አስጨራሽ ጉዞ እና የእህቱን ታላቅ ድጋፍ በዝርዝር አስታውሷል። ዲዮማንዴ በወጣትነቱ በበርካታ የዓለም ታላላቅ ክለቦች ማለትም በቼልሲ፣ በክሪስታል ፓላስ፣ በሬንጀርስ እና በኦሊምፒያኮስ የሙከራ እድል አግኝቶ እንደነበር ያስታወሰ ሲሆን፤ በወቅቱ ተስፋ ሰጪ ተጫዋች ቢሆንም ባልታወቁ ምክንያቶች ግን የትኛውም ክለብ ሊያስፈርመው አልቻለም።

​የቪዛ ጊዜው በማለቁ ምክንያት ተስፋ ቆርጦ ወደ አፍሪካ ሲመለስ፣ እህቱ ብቻ እንደነበረች እና ተስፋ እንዳልቆረጠችበት በጽሁፉ ገልጿል። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለስፔኑ ሌጋኔስ መፈረሙን ተከትሎ አብረው እንባ እንደተራጩ የሚያስታውሰው ተጫዋቹ፤ “ከእህቴ ሞት በኋላ ግን ምንም አይነት ስሜት የለኝም፤ ህይወት ባዶ ሆኖብኛል” ሲል በለቅሶ የታጀበ ስሜቱን አስፍሯል።

​በእግር ኳስ ሜዳ ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ ለእህቱ ክብር እንደሆነ የገለጸው ዲዮማንዴ፣ ስሟ በዓለም እንዲታወቅ እና በልቡ ውስጥ ለዘላለም እንድትኖር ለማድረግ እንደሚጥር በአጽንኦት ተናግሯል። የያን ዲዮማንዴ ይህ አሳዛኝ የህይወት ታሪክ፣ እግር ኳስ ከሜዳው ባሻገር ምን ያህል ጥልቅ ስሜታዊ ታሪኮችን እንደሚሸከም ማሳያ ሆኗል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: