#Ethiopia | የ6ኛ ዓመት ማጠናቀቂያ ልዩ የክረምት ንቅናቄ
“Reading really matters!”
የ”ሐዋሳ ታነባለች” የንባብ ባህል ማጎልበቻ ፕሮጀክት የተመሰረተበትን 6ኛ ዓመት በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ጉዞ ምክንያት በማድረግ፣ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወቅትን በልዩ የንባብ ልምድና ንቅናቄ ለማሳለፍ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።
የክረምቱን የንባብ ንቅናቄ ይበልጥ ለማድመቅና ማህበረሰባችንን ለማነቃቃት፣ የእርሶ ተሞክሮ ለብዙዎች ብርሃን ይሆናል ብለን እናምናለን።
እርስዎም
በትውልዱ ውስጥ የንባብ ባህልን ለማስረፅ በምናደርገው በዚህ ጥረት ላይ አሻራዎን ያኖሩ ዘንድ—”የምንግዜም ምርጥ 3 መጽሐፍትዎን” እና አጭር ምክርዎን እንዲያጋሩን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። ለወጣቱ በአርአያነት የሚጠቀሱ ምሁራንና ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን
የተሳታፊዎች ምርጫና ተሞክሮ ከሰኔ 15 እስከ ሰኔ 30 ድረስ ባሉት ቀናት፦
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን እና
በሐዋሳ ኤፍኤም 100.9 (Hawassa FM 100.9) ለሰፊው ማህበረሰብ የሚተላለፍ ይሆናል።
የክረምት እረፍትን በዕውቀት እንሙላው፤ የንባብ ባህልን አብረን እናሳድግ!
“ሐዋሳ ታነባለች የንባብ ባህል ማጎልበቻ ፕሮጀክት — 6ኛ ዓመት ልዩ ማስታወሻ”
Source: GetuTemesgen








No comments yet.