መረጃ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀጣዩ በጀት ዓመት 502 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት አቀረበ።
ረቂቅ በጀቱ ከዘንድሮው በጀት የ43 በመቶ ብልጫ አለው።
ከበጀቱ ውስጥ፣ 71 በመቶው ለድህነት ቅነሳ እና ከዘላቂ ልማት ግቦች ጋር የተያያዙ እቅዶችን ለማሳካት እንደሚውል ተገልጧል።
በጀቱ፣ የልማት ስትራቴጂዎችን፣ የነዋሪዎችን የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት አቅርቦት ማሳደግን በተለይም መንገድን፣ ውሃን፣ መኖሪያ ቤትን፣ ጽዳትን፣ ትራንስፖርትንና የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልን እንዲሁም ትምህርትን፣ ጤናን እና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች የሚደረግ ድጎማን ጨምሮ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ማሻሻልን ታሳቢ ያደረገ መኾኑን አስተዳደሩ አስታውቋል።
በተያዘው በጀት ዓመት የፌደራል ድጎማ ያላተመደበላት ከተማዋ፣ በቀጣዩ የፌደራሉ መንግሥት በጀት 74 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ተይዞላታል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.