#Ethiopia | አሜሪካ በአፍሪካ ትልቁና እስካሁን ያልተነካውን የኬንያ የባዮኒየም እና የሪር አርዝ የማዕድን ክምችት ለመጠቀም የሚያስችላትን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት መፈራረሟ ተገለጸ። ወደ 62.4 ቢሊዮን ዶላር (9.7 ትሪሊዮን የኬንያ ሽልንግ) ግምት ያለው ይህ ስምምነት፣ ዋሺንግተን ከቤጂንግ ጋር በስትራቴጂካዊ ማዕድናት ይዞታ ላይ ለምታደርገው ከባድ ፉክክር ትልቅ ስኬት እንደሆነ ተነግሯል።
በኬንያው ምሪማ ሂል አካባቢ የሚገኘውን ይህንን እምቅ የማዕድን ሀብት ለማልማት የተደረገው አዲሱ ስምምነት ማዕድናቱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ውጭ ከመላክ ይልቅ በኬንያ ሀገር ውስጥ እንዲቀነባበሩና እሴት እንዲጨመርባቸው የሚያስገድድ ነው። ይህም ቀደም ሲል ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ ወደ ውጭ የመላክ የነበረውን የተለመደ አሰራር የሚቀይር መሆኑ ታውቋል።
ይህ የአሜሪካ እርምጃ የመጣው ለንጹህ ኢነርጂ እና ለላቁ ቴክኖሎጂዎች እጅግ ወሳኝ በሆኑት የአፍሪካ ወሳኝ ማዕድናት ላይ ከቻይና እና ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ዓለም አቀፋዊ ፉክክር በበረታበት ወቅት ነው።
በአሁኑ ወቅት ቻይና ከአፍሪካ የሚወጡ ማዕድናትን በማቀነባበር እና በማቅረብ ረገድ ቀዳሚዋ ሀገር ብትሆንም አሜሪካ ግን የአቅርቦት ዋስትናን ለማረጋገጥና በሀገር ውስጥ እሴት የመጨመር ስራን ለመደገፍ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በስፋት እየተገበረች ትገኛለች።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.