የውጭ ዜጎችን በማገት ገንዘብ የጠየቁ 3 ፓኪስታናውያን

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን በመያዣነት በመጠቀም ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የጠየቁ ሦስት የፓኪስታን ዜጎች በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ዝሻን ካሊድ፣ ፍርዝ መሃመድ እና መሀመድ ጀናይድ ሲሆኑ፣ ወንጀሉን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አትሌቶች መንደር በተከራዩት መኖሪያ ቤት ውስጥ መፈጸማቸው ተገልጿል።

እንደ ፖሊስ መረጃ፣ ተጠርጣሪዎቹ የህንድና የባንግላዴሽ ዜጎችን በማገት በገመድ በማሰርና አፋቸውን በፕላስተር በማፈን ከ15 እስከ 30 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ጥያቄ አቅርበውባቸዋል።

በተጨማሪም ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ አራት የህንድ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ ከ15 ሺህ እስከ 25 ሺህ የህንድ ሩፒ እንዲሰጡ ጫና ማሳደራቸውን ተበዳዮቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አስረድተዋል።

የወንጀሉ መረጃ ከደረሰ በኋላ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ከፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ እና የመያዣ ትዕዛዝ በመፈጸም ባደረገው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውሏል።

በወቅቱም ለወንጀሉ ጥቅም ላይ ውለዋል የተባሉ ቢላዋዎች፣ ገመዶች፣ ፕላስተሮች እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦች መያዛቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለጉዳዩ መረጃ በመስጠት ለተባበሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፣ ሕብረተሰቡም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲያስተውል ለፖሊስ ፈጣን መረጃ እንዲያደርስ ጥሪ አቅርቧል።

Via ዋና ሳጅን አዳነ ደስታ – አ/አ ፖሊስ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: