በኤልኒኖ ተፅዕኖ ምክንያት በመላው ሀገሪቱ የተለያየ መጠን ያለው የክረምት ዝናብ እና ከፍተኛ የሙቀት መጠን እየተመዘገበ መሆኑን…

- Advertisement -
Sidebar AD
በኤልኒኖ ተፅዕኖ ምክንያት በመላው ሀገሪቱ የተለያየ መጠን ያለው የክረምት ዝናብ እና ከፍተኛ የሙቀት መጠን እየተመዘገበ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ካለፉት ቀናት ጀምሮ በሀገሪቱ በአብዛኞቹ አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት የነበረ ሲሆን፤ከቀላል እስከ መካከለኛ እንዲሁም ከ30-1መቶ25 ሚሊ ሜትር የሚደርስ እጅግ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ መመዝገቡን የኢንስቲትዩቱ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ለኢትዮ ኤፍ ኤም  ገልፀዋል፡፡
ይህ በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው የዝናብ መጠንና ስርጭት ለግብርና ስራ እንቅስቃሴ፣ ለማዳበሪያ ዝግጅት፣ ለውሃ ተፋሰሶች ልማት እንዲሁም ለቋሚ ተክሎች ፍላጎት መሟላት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የክረምቱ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በእነዚህ አካባቢዎች ዝናብ እየጣለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍሎች፣ በጋምቤላ፣ በመተማ፣ በቋራ፣ በአፋር፣ በሰመራ፣ በዱፍቲ፣ በቀብሪደሃር እና በጎዴ አካባቢዎች የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ መመዝገቡን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።
ሰላማዊት ዲታ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1