አብረው ለመስራት ተስማሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | በኢትዮጵያ የስፖርትና የቱሪዝም ዘርፍ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንደሚኖረው በሚጠበቀው የመጀመሪያው ከፍተኛ ደረጃ የMMA (Mixed Martial Arts) ውድድር ላይ ትብብር ለመፍጠር፣ Sweat Box እና Kuriftu Resorts የመግባቢያ ስምምነት (MOU) አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ በከፍተኛ ዝግጅት የሚካሄደው ግዙፉ የ”MMA” (Mixed Martial Arts) ውድድር፣ ለስኬታማነቱ ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር ዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ስትራቴጂያዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

​የMMA ውድድር ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

ውድድሩ በሀገሪቱ የቱሪዝም እና የመዝናኛ ዘርፍ አቅም ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ተፅዕኖ በመገንዘብ፣ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በስምምነቱ መሰረት ተወዳዳሪዎች ለ1 ወር በኩሪፍቱ ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን ስምምነቱ ለአንድ አመት እንደሚቆይ ተነግሯል።

​ስምምነቱ የMMA ተወዳዳሪዎች በኩሪፍቱ ሪዞርቶች ልዩ ቅናሾችን እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በጋራ የጤና እና ደህንነት ፕሮግራሞችን፣ ሀገራዊ የጤና ንቅናቄዎችን እና የተለያዩ ስፖርታዊ ኩነቶችን ለማዘጋጀት መንገድ ይከፍታል።

እንደዚሁም ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሥራት በሀገሪቱ የስፖርትና የጤና (Wellness) ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ለመፍጠር አቅደዋል።

በዚህም መሠረት የጋራ የጤናና ደህንነት ፕሮግራሞችን፣ ሀገር አቀፍ የጤና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎችን እና የተለያዩ የስፖርት ዝግጅቶችን በጋራ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Kurifturesort
#SweatBox
#ጌጡተመስገን
#ሚዲያኮሚኒኬሽን
#Getutemesgen
#Mediacommunication






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2