#Ethiopia | አዲስ አበባ – በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለበርካታ ዓመታት ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አዘጋጅነት በተለያዩ የሙያ ደረጃዎች ያገለገሉት አንጋፋው ጋዜጠኛ Daniel Tadesse በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ታኅሣሥ 26 ቀን 1959 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከአባታቸው ታደሰ ዳምጠው እና ከእናታቸው ፈለቀች ዳኜ ተወልደዋል።
ከታኅሣሥ 18 ቀን 1994 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተለይም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ውስጥ ለ24 ዓመታት በሪፖርተርነት፣ በአዘጋጅነት እና በከፍተኛ የሙያ ኃላፊነቶች አገልግለዋል።
በሙያ ዘመናቸውም ለሕዝብ ትክክለኛና ተደራሽ መረጃ በማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ይታወሳል።
የሟቹ ሥርዓተ ቀብር ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ጀምሮ በKidist Lideta Maryam Church እንደሚፈጸም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በጋዜጠኛው ህልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሙያ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።
ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ነፍስ ይማር። 🕊️


Source: GetuTemesgen









No comments yet.