#Ethiopia | ከተመሠረተ 25 ዓመታትን ያስቆጠረው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ISO 15189:2022 የህክምና ላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት የምስክር ወረቀት አግኝቷል።
የሆስፒታሉ መስራች እና ባለቤት እንዲሁም ስራ አስኪያጅ የሆኑት ደ/ር ፍቅረማሪያም ጉድታ እንደተናገሩት ይህ ምዕራፍ ሆስፒታሉ ከ250 በላይ አለም አቀፍ የላቦራቶሪ የጥራት መስፈርቶችን ማሟላቱን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ለታካሚዎች የላቀውን እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ሆስፒታሉ ያሳየውን ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
የላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ስርዓት በሆስፒታል ላቦራቶሪ ውስጥ ሁሉንም ሂደቶች መደበኛ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው እንዲሆን የሚያደርግ ሆኖ የተዋቀረ ነውም ብለዋል።
ሆስፒታሉ ያሟላቸው ቁልፋ የጥራት መስፈርቶች የላቦራቶሪው የጥራት ቁርጠኝነት ፣ሰነድ አስተዳደር የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ብቃት እና ሌሎችም ይገኙበታል።
የኢፌድሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት ሬጉላተሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ያደረገው ተቋማዊ ግንባታ አስደናቂ መሆኑን ገልፀው ለተወዳዳሪነት አክሪዲቴሽን መሠረታዊ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ሚኒስትር ዲኤታው ገለፃ ኢኖቬሽን በዛሬ ዘመን ዋና ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ተቋማትም በቴክኖሎጂ ታግዘው ሥራቸውን በጥራትና በተወዳዳሪነት መሥራት አለባቸው ብለዋል።
ተቋሙ በአለም ለ19ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ የተከበረውን የአለም የአክሪዲቴሽን ቀን ዘንድሮ ሰኔ 15 2018 “አክሪዲቴሽን ለፈጠራ እምነት እና ዘላቂነት በሚል ቃል በዓሉን አክብሯል።
በዕለቱም ፍቅረሰላም ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትም የምዘና ብቃት ማረጋገጫ እንዳገኙ ታውቋል።
“ወርቃማ ልቦች ፣ አገልጋይ እጆች !” በሚል መርህ ከክሊኒክ አንስቶ እስከ አጠቃላይ ሆስፒታል 25 ዓመታት የዘለቀው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ነው።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ፍቅረሰላምሆስፒታልሆስፒታል
#የንግድናቀጠናዊትስስርሚኒስትር
#ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን
#Getutemesgen #Mediacommunication



Source: GetuTemesgen









No comments yet.