ኢዜማ በ7ኛዉ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ 86 መቀመጫዎችን በማግኘት ቀዳሚዉ ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ማጠናቀቁን ገለፀ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ ኢዜማ ሀገር አቀፉ ምርጫዉ ከነእንከኖቹም ቢሆን በሰላም በመጠናቀቁ ደስተኛ ነኝ ሲል መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ይህን ተከትሎም ፓርቲዉ ለውድድር በቀረበባቸው ቦታዎች 13 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና 73 የክልል እና የከተማ ምክር ቤት ወንበሮችን በድምሩ 86 መቀመጫዎችን በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚው ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ማጠናቀቁን አስታዉቋል።
ኢዜማ ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ባሉት ዓመታት ጠንካራ ጎኖቹን በማስቀጠል እንዲሁም የነበሩበትን ክፍተቶች በስትራቴጂ እና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራት በመሙላት ተጨባጭ የተፎካካሪ ፓርቲነት ሚናውን ጊዜ ሳያባክን የሚጀምረው ተግባር መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ፓርዉ አክሎም ገዢ ሆኖ እንዲቀጥል ለተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ እና ለውድድሩ ተሳታፊዎች የእንኳን ደስያላችሁ መልዕክቱን አሥተላልፏል፡፡
በተጨማሪም አሸናፊው ፓርቲ ከዛሬ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባትና ፍትሐዊ የፖለቲካ ምህዳርን ለሁሉም እኩል ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲሠራ፤ አማራጭ ሃሳቦችን እንዲሰማ፤ እንዲሁም ትችቶችን በሆደ ሰፊነት እያስተናገደ የሀገሪቱን ዴሞክራሲ በጋራ ለመገንባት ቁርጠኛ እንዲሆን ጥሪዉን አቅርቧል፡፡
@Seledadotio

No comments yet.