#Fastmereja- “አክሪዲቴሽን ለፈጠራ፣ እምነት እና ዘላቂነት” በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ለ16ኛ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ19ነኛ ጊዜ የዓለም አክሪዲቴሽን ቀን በዛሬው ዕለት (ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም) በልዩ ድምቀት ተከብሯል።
ይህ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተከበረው ደማቅ በዓል ላይ፤ ላለፉት 25 ዓመታት በሕክምናው ዘርፍ ታማኝ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትም ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የ ISO 15189:2022 የሕክምና ላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ስርአት እዉቅና አግኝተዋል።
የሆስፒታሉ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ፍቅረማርያም ጉድታ በበዓሉ ላይ እንደገለጹት፤ ይህ እውቅና ሆስፒታሉ ከ250 በላይ ዓለም አቀፍ ጥብቅ መስፈርቶችን አሟልቶ በመገኘቱ የተሰጠ ስጦታ መሆኑን ገልፀዋል።
ሆስፒታሉ ያሟላቸው ቁልፋ የጥራት መስፈርቶች የላቦራቶሪው የጥራት ቁርጠኝነት ፣ሰነድ አስተዳደር( Control document)፣ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ብቃት ማረጋገጥ፣ የመሳሪያዎች ብቃትን ማረጋገጥ ፣ የናሙና አያያዝ፣ የናሙና አውሰድ፣ ማጓጓዝ፣ ማከማቸት እና መለየት፤ የውጤት ትክክለኛነትና አስተማማኝነት እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
የላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ስርዓት በሆስፒታል ላቦራቶሪ ውስጥ ሁሉንም ሂደቶች መደበኛ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው እንዲሆን የሚያደርግ ሆኖ የተዋቀረ አስተዳደራዊ ስርዓት ሲሆን ይህም ሥርዓት በተለይበዓለም አቀፍ መስፈርቶች (እንደ ISO 15189 መሠረት የተዘጋጀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር195/2003 መቋቋሙ ተገልጿል።
አገልግሎቱ ተጠሪነቱ ለንግድና ቀጠናዊ ትስስርሚኒስቴር ሆኖ በህክምና iso 15189 እና በፍተሻ ላቦራቶሪiso/ ies 17028፣በሰርተፊኬሽን iso/ies 17065 f iso/ies 17024 እንዲሁም በኢንስፔክሽን iso/ies 1702ዐ ሥራ ላይለተሠማሩ የተስማሚነት ምዘና ተቋማት ብቃታቸውን በማረጋገጥ የአክሪዲቴሸን አገልግሎት በመስጠት የተቋማቱን አገልግሎቶች እና የሚያመርቱት ምርቶች ላይ ተጠቃሚውም ሆነ አምራቾች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ አለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን ዘርግቶ በተጠናከረ መልኩ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ (ሲኤምሲ ሚካኤል ፊትለፊት) የሚገኘውና የዚህ ታላቅ በዓል ደማቅ ታሪክ ተጠቃሽ የሆነው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል፤ ለ250 ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ከጠቅላላ ቀዶ ሕክምና እስከ ፕላስቲክ ሰርጀሪና የካንሰር ሕክምና ድረስ ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።



Source: FastMereja









No comments yet.