7 ወንበሮች አልረከብም!

- Advertisement -
Sidebar AD

– ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት

#Ethiopia | በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአዲስ አበባ፣ በአማራና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በድምሩ ሰባት የምክር ቤት ወንበሮችን (ሁለት የሕዝብ ተወካዮች እና አምስት የክልል ምክር ቤት) ያሸነፈው ‘ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት’ ቅንጅት፣ ያገኘውን መቀመጫ እንደማይረከብና ምክር ቤት እንደማይገባ ለቢቢሲ አስታወቀ።

ምርጫውን “የጨረባ” ሲሉ የገለጹት የቅንጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌትነት ወርቁ፣ በአገሪቱ ያለው የሰላም እጦትና “ጠባብ” የፖለቲካ ምኅዳር ለውሳኔያቸው በዋና ምክንያትነት ጠቅሰዋል።

መንግሥት ወደ ንግግርና ድርድር እስኪመጣ ድረስ ዕውቅና እንደማይሰጡት የገለጹት ኃላፊው፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብም ለምርጫው ዕውቅና እንዳይሰጥ ቅስቀሳ እያደረጉ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

ይህ ውሳኔ ለመረጣቸው ሕዝብ ድምፅ መንፈግ እንዳልሆነ የገለጸው ጥምረቱ፣ ምክር ቤት አለመግባትን ‘እንደ መደራደሪያ መሣሪያ’ እየተጠቀመበት መሆኑንና መንግሥት ጦርነትን ማቆም፣ እስረኞችን መፍታትና የፖለቲካ ምኅዳርን ማስተካከል የመሳሰሉ ቅድመ ሁኔታዎችን ተቀብሎ ቀና ምላሽ ከሰጠ ውሳኔያቸውን ሊቀለብሱ እንደሚችሉ አመልክቷል።

ኢሕአፓ፣ መኢአድ እና እናት ፓርቲን ጨምሮ አምስት ፓርቲዎችን ያቀፈው ይህ ጥምረት፤ ተመራጮቹ የፓርቲውን ውሳኔ ጥሰው ወደ ምክር ቤት የሚገቡ ከሆነ የሞራልና የሕግ ኃላፊነት እንደሚጠይቃቸው አስጠንቅቆ፣ ከፓርቲ ማባረርን ጨምሮ ጠንካራ የሥነ-ምግባር እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳስቧል።

#ኢትዮጵያ #የምርጫውጤት #ትብብርለኢትዮጵያአንድነት #ፖለቲካ #ሰበርዜና #Ethiopia #EthiopianPolitics


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: