“ቤት ያላገኘ ተፈናቃይ ካለ ሥልጣኔን እለቃለሁ” — አቶ ግርማ ሰይፉ
የአዲስ አበባ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በከተማዋ በነበረው የኮሪደር ልማት ምክንያት ተፈናቅሎ ምትክ ቤት ወይም መሬት ያላገኘ አንድም ሕጋዊ ሰው አለመኖሩን አስታወቁ።
ካርታ ወይም የቀበሌ ቤት ኖረውት ምትክ ያጣ ሰው ካለ በገዛ ፈቃዳቸው ከሥልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ ልማቱ ለሀገር ጥቅም የተሠራ መሆኑን ገልጸው፤ ሆኖም ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በደል የደረሰባቸው ወገኖች መኖራቸውን አልሸሸጉም።
በሌላ በኩል፣ የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ ዘመናዊነትና ውበት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም፤ በሂደቱ ወቅት በቂ ዝግጅት፣ ግልጽነትና ተመጣጣኝ ምትክ አላገኘንም የሚሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታዎች በተደጋጋሚ ሲነሱ መቆየታቸው ይታወቃል።
@Seledadotio

No comments yet.