የውጭ ሀገር ዜጎችን በማገት ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የጠየቁ ሦስት ፓኪስታናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ
የፓኪስታን ዜግነት ያላቸው ዝሻን ካሊድ፣ ፍርዝ መሃመድ እና መሀመድ ጀናይድ የተባሉ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሰኔ 4 እና ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አትሌቶች መንደር ነው።
ተጠርጣሪዎቹ በተከራዩት የመኖሪያ ቤት ውስጥ የህንድና የባንግላዴሽ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች በመያዣነት በመጠቀም የግል ተበዳዮችን በገመድ በማሰርና በፕላስተር በማፈን ከ15 እስከ 30 ሚሊየን ብር በመጠየቅ ጥቃት አድርሰውባቸዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በዚህ ብቻ ሳያበቁ ሰኔ 11ቀን 2018 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የገቡ 4 የህንድ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ ከ15 እስከ 25 ሺህ የህንድ ሩፒ አስልኩ በማለት ድብደባ ሲፈጽሙባቸው እንደነበር የግል ተበዳዮች ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
የወንጀሉ መፈጸም መረጃ የደረሠው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ተገቢውን የፍርድ ቤት መያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባከናወነው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀሙበት ከነበረው ቢላዋ፣ ገመድና ፕላስተር እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.