ኬፕ ቨርዴ ሁለተኛ ነጥቧን ስታገኝ፤

- Advertisement -
Sidebar AD

ግብፅ በዓለም ዋንጫ ታሪኳ የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች

#Ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር አፍሪካዊቷ ደሴት ሀገር Cape Verde በምድብ ስምንት ሁለተኛ ነጥቧን አግኝታለች። ኬፕ ቨርዴ ከሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን Uruguay ጋር 2–2 አቻ በመውጣት ያለመሸነፍ ጉዞዋን ቀጥላለች።

በጨዋታው ለኬፕ ቨርዴ ኬቪን ፒና እና ሀሊዮ ቫሬላ ግቦችን ሲያስቆጥሩ፣ ለኡራጓይ ደግሞ ማርከስ አራውሆ እና ማቲያስ ኦሊቬራ ከመረብ አሳርፈዋል። ኬፕ ቨርዴ በሁለት ነጥብ ወደ ጥሎ ማለፉ የመሸጋገር ተስፋዋን አጠናክራለች።

በሌላ የምድቡ ጨዋታ Belgium እና Iran ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

በተመሳሳይ ጊዜ Egypt በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች። ግብፅ ከ New Zealand ጋር ባደረገችው ጨዋታ በመጀመሪያ ተከትላ ብትቆይም፣ በሙስጠፋ ዚኮ፣ Mohamed Salah እና ማህሙድ ትርዝጌት ግቦች 3–1 በማሸነፍ ታሪካዊ ድል አግኝታለች።

ድሉ ግብፅን በአራት ነጥብ የምድቧ መሪ እንድትሆን አድርጎ ወደ ጥሎ ማለፉ የመድረስ ዕድሏን አስፋፍቷል።።




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: