#Ethiopia | የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በአሜሪካ ከሚገኘው ሊበርቲ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት አመራር (Educational Leadership) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቀቁ።
ብፁዕነታቸው ይህንን የትምህርት ማዕረግ በስኬት በማግኘታቸው በበላይ ሊቀ ጳጳስነት የሚመሩት የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ለፕሬዝዳንቱ የተሰማውን ጥልቅ ደስታ በይፋ ገልጿል።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ በስፋት የሚታወቁ ሲሆን ከዚህ ቀደም በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማዘጋጀትና በማሳተም እንዲሁም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በመምህርነትና በአስተዳደር ኃላፊነት የላቀ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩና አሁንም በማገልገል ላይ የሚገኙ ምሁር አባት ናቸው።
ከዚህም ባለፈ ባከናወኗቸው ሰፊ አካዳሚያዊ ተግባራትና ተከታታይ አገልግሎቶች ምክንያት ላለፉት ዓመታት የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ማግኘታቸው ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያስታውሳል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.