#Ethiopia | የፈረንሳዩ ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል ኢነርጂስ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የነዳጅ ማደያዎች ለኦላ ኢነርጂ በመሸጥ ከሀገሪቱ የነዳጅ ችርቻሮ ገበያ ሊወጣ መሆኑ ተዘግቧል።
‘ብር ሜትሪክስ’ እንዳስነበበው ሁለቱ ተቋማት ወደ 120 የሚጠጉ የቶታል ነዳጅ ማደያዎችን ሽያጭ በተመለከተ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ሆኖም የሽያጩ የገንዘብ መጠን እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ኩባንያዎቹም ስምምነቱን እስካሁን በይፋ አላረጋገጡም።
ከፈረንጆቹ 1950 ጀምሮ በኢትዮጵያ ምርትና አገልግሎቱን ሲያቀርብ የቆየው ቶታል ኢነርጂስ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ የችርቻሮ ገበያውን ለማስተካከል ከያዘው ስትራቴጂ አኳያ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ ሽያጭ በሕግ አግባብ ጸድቆ ከተጠናቀቀ ቀድሞ ‘ኦይልሊቢያ’ በመባል የሚታወቀውና በመላው አፍሪካ ሰፊ ተደራሽነት ያለው ኦላ ኢነርጂ በኢትዮጵያ የነዳጅ ሥርጭት ገበያ ላይ ያለውን ድርሻና አቅም በእጅጉ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.