ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣው የሸቀጦች ዋጋ በበለጠ ከመንግስት ለሚያገኙት አገልግሎት የሚከፍሉት ክፍያ እየፈተናቸው ነ

- Advertisement -
Sidebar AD

ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣው የሸቀጦች ዋጋ በበለጠ ከመንግስት ለሚያገኙት አገልግሎት የሚከፍሉት ክፍያ እየፈተናቸው ነው ተባለ።

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስት አገልግሎቶች ላይ የሚታየው የታሪፍ ማሻሻያ እና ተገልጋዩ አገልግሎት ለማግኘት የሚጠየቀው ወጪ ከፍተኛ መሆን የነዋሪውን ኑሮ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎበታል።

በዚህ ምክንያትም የሸማቹ መብት እየተጣሰ በመሆኑ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተናግሯል።

የመንግሥት አገልግሎቶች ትርፍ ማጋበሻ ሳይሆኑ ዜጎችን ለመደገፍ፣ ማኅበራዊ ፍትሕን ለማረጋገጥና በሕግ የተጣሉ ግዴታዎችን ለመወጣት የሚቀርቡ መሠረታዊ አገልግሎቶችና መብቶች ቢሆኑም በአሁኑ ወቅት በጅምላ እየታዩ ያሉ የዋጋ ጭማሪዎች ሸማቹን ማኅበረሰብ ተስፋ የሚያስቆርጡ፣ ወደ ከፋ ድህነት የሚገፉና ዜጎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ በማድረግ በሚከፍሉት ግብር የመገልገል የዜግነት መብታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ብሏል ድርጅቱ፡፡

የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ያደረጓቸው የዋጋ ጭማሪዎች የማክሮ-ኢኮኖሚውን ሕመምና የሕዝቡን የደመወዝ ወለል ያላገናዘቡ፣ የሸማቹን ኪስ ሙሉ በሙሉ የሚያራቁቱ መሆናቸውን ያነሳ ሲሆን ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአዲስ ፓስፖርት ክፍያ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ዋጋ፣ የቴሌኮም አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች ላይ የታወጣን ጭማሬ እንደማሳያ አንስቷል፡፡

በእነዚህ እና በሌሎች የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ጭማሬዎች አገልግሎት ፈላጊው ማህበረሰብ እየፈተነው እንደሆነ ተመልክተናል ሲል የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተናግሯል፡፡

ዘገባው የሸገር ሬዲዮ ነው


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: