#Fastmereja:- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በምግብ ምዝገባና ፈቃድ መሪ ስራ አስፈጻሚ ስር ለሚገኘው የምግብ አምራቾች ቅድመ ፈቃድ ኢንስፔክሽን ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ISO/IEC 17020:2012 እውቅና ማግኘቱን አስታወቀ።
በዕውቅና ሰነዱ ላይ እንደተገለፀው ባለስልጣኑ በምግብ ዘርፍ የሚያካሂደው የቅድመ ፈቃድ ኢንስፔክሽን በዓለም አቀፍ መስፈርት መሰረት ደረጃን ያሟላ መሆኑ ተረጋግጧል።
እውቅናው አጠቃላይ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ምግቦች ቁጥጥር፣ለልዩ የአመጋገብ አገልግሎት የሚውሉ ምግቦች አምራቾች ቁጥጥር (ኢንስፔክሽን) እና ለአጠቃላይ አነስተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ምግቦች አምራቾች ቁጥጥር የሚውል የቅድመ ፈቃድ ኢንስፔክሽንን ያጠቃለለ ሲሆን ይህ ታሪካዊ ዕውቅና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዘርፉ የሚሰጣቸው የቁጥጥር ስራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትና እምነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ሲሆን የሀገር ውስጥ የምግብ ምርቶች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትልቅ በር ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።
ባለስልጣኑ
ለዚህ ስኬት መገኘት አስተዋጽዖ ላበረከቱ አመራርና ባለሙያዎች ምስጋናውን አቅርቧል።


Source: FastMereja









No comments yet.