በኢትዮጵያ የስፖርት ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት የሚችል የመጀመሪያው አገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

በኢትዮጵያ የስፖርት ዘርፍ ታሪክ አዲስ የኢንዱስትሪ ዕንቅስቃሴ ለመጀመር እና ስፖርትን ከመዝናኛነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ምንጭነት ለማሸጋገር ያለመ ታላቅ አገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ።

ይህንን በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን ታላቅ ኹነት ያዘጋጁት አዱሊያን ማስታወቂያ እና ዳይመንድ ማርኬቲንግ ኤንድ ኮሚኒኬሽን ሲሆኑ፣ ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ስፖርት ከባሕላዊ የሩጫ እና የእግር ኳስ ማዕቀፍ አውጥቶ ወደ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የንግድ ትስስር እና የኢንዱስትሪ ምርታማነት የሚያሸጋግር የለውጥ ምዕራፍ እንደሚሆን አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

ይህ አውደ ርዕይ እና አገራዊ መድረክ በርካታ ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎችን ይዞ የሚቀርብ ሲሆን፣ የስፖርት ዕቃ አምራቾችን፣ አከፋፋዮችን፣ ስፖርተኞችን እና የስፖርት ማሕበራትን በአንድ መድረክ በማገናኘት የአገር ውስጥ ምርትን ማበረታታት እና የገበያ ትስስር መፍጠር፤ በዓለም ላይ ያሉ ዘመናዊ የስፖርት ስልጠና ቴክኖሎጂዎችን (Digital Sports Solutions)፣ የስፖርት ሕክምና፣ አመጋገብ እና ሳይንስ ላይ ያተኮሩ የውይይት መድረኮችን ለኢትዮጵያ ስፖርተኞችና አሰልጣኞች ማስተዋወቅ፤ ወጣቶች እና ቤተሰቦች በአካል ተገኝተው የተለያዩ የስፖርት አይነቶችን እንዲሞክሩ በማድረግ፣ በአካላዊ ብቃት፣ በእንቅስቃሴ እና በጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ላይ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር እንዲሁም የስፖርት ዝግጅቶችን በንግድ መልክ በማደራጀት ለሀገር ውስጥ አምራቾች ሰፊ እድል መስጠት፤ ይህም የውጭ ምንዛሪ ወጪን በመቀነስ የአገር ውስጥ አቅምን ለመገንባት እና ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።

### ለሀገር የሚሰጠው ስልታዊ ጠቀሜታ

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፖርቱ መስክ የጎላ ዝና ያላት ቢሆንም፣ ይህንን እውቅና ወደ ስፖርት ኢንዱስትሪ ለመቀየር የሚያስችል የተቀናጀ የንግድ እና የልውውጥ መድረክ ክፍተት እንደነበረበት ይነገራል። ዳይመንድ ማርኬቲንግ እና አዱሊያን ማስታወቂያ ይህንን ክፍተት በመሙላት የኢትዮጵያን ስፖርት ከ”ሞያ” ወደ “ኢንዱስትሪ” ለማሸጋገር አቅኚ የለውጥ ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዝግጅቱ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን (MDF-based) የኤግዚቢሽን ስታንዳርዶችን የሚጠቀም በመሆኑ፣ ለወደፊት በሀገሪቱ ለሚካሄዱ ስፖርታዊ ኹነቶች አዲስ የጥራት ደረጃ (Benchmark) ያስቀምጣል። ይህም ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፖርት አስተናጋጅነት (Sports Event Hub) እንድትታወቅ በማድረግ ረገድ ለስፖርት ዲፕሎማሲው ትልቅ አጋዥ እንደሚሆን ታምኖበታል።

ኩባንያዎቹ ከዚህ ቀደም መሰል ዝግጅቶችን የማካሄድ ልምድ እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማሕበር ጋር በመተባበር “የአመለካከት እና አስተሳሰብ ለውጥ ኤግዚቢሽን” እንዲሁም ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር በጃን ሜዳ “የባሕል እና ስፖርት ፌስቲቫል” በተሳካ ሁኔታ ማከናወናቸውን አስታውሰዋል።

ለተሳታፊዎች እና ለጎብኚዎች ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፣ እያንዳንዱ የኤግዚቢሽን ቦታ (Zone) በዓለም አቀፍ የደሕንነት መመዘኛዎች መሰረት እንደሚዋቀር ተገልጿል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከፌዴሬሽኖች፣ ከጤና ባለሞያዎች እና ከሚመለከታቸው የደህንነት አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ላይ መሆናቸውንና የህክምና እና የድንገተኛ አደጋ ዝግጅቶች በተሟላ ሁኔታ እንደሚቀርቡ አዘጋጆቹ አረጋግጠዋል።

ይህ አገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽን የአንድ ጊዜ ክስተት ብቻ ሆኖ እንደማይቀረና ዋና ዓላማው በየዓመቱ የሚካሄድ ብሔራዊ የስፖርት ክብረ በዓል (Annual Sports Exhibition) ማድረግ መሆኑ ተገልጿል። የዘንድሮውን የመጀመሪያ ዝግጅት ስኬት እንደ ግብዓት በመጠቀም፣ በቀጣይ ዓመታት የክልል እና የዓለም አቀፍ ተሳታፊዎችን በማካተት ዝግጅቱን ይበልጥ ለማስፋት ታቅዷል።






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: