የዓለም ትልቁ የጎል ማሽን ሃሪ ኬንን ከዜሮ ሜትር አድንዝዞት ያመሸው ጠንቋይ !ከሁለት ቀናት በፊት ጋናዊው ጠንቋይ ናና ክዋኩ …

- Advertisement -
Sidebar AD
የዓለም ትልቁ የጎል ማሽን ሃሪ ኬንን ከዜሮ ሜትር አድንዝዞት ያመሸው ጠንቋይ !

ከሁለት ቀናት በፊት ጋናዊው ጠንቋይ ናና ክዋኩ ቦንሳም “በሃሪ ኬን ላይ እየሰራሁ ነው። ከዚህ በፊት ምን ማድረግ እንዳለብኝ አሳይቻለሁ ስለዚህ እሱን ለማስቆም ምን አይነት ስራ መስራት እንዳለብኝ አውቃለሁ። ጋናን ለመርዳት ስራዬን እሰራለሁ።”ብሎ መናገሩን ግዮን ማለዳ ከቀናት በፊት አሳውቀን ነበር
የጋና “ጁጁ” ሰርቷል ቢባል ማጋነን አይሆንም እጣኑም ፣ ጭሱም፣ አመዱም፣ ዱቄቱም፣ ጨሌውም… ምኑም አልቀረም፤ የዓለም ትልቁ የጎል ማሽን ሃሪ ኬንን ከዜሮ ሜትር ላይ አደንዝዞታል።
ጥቋቁሮቹ ክዋክብት (Black Stars) ግልፅ ፔናሊቲ ጭምር እየተከለከሉ፣ የእንpግሊዝን ክንድ ገትረው በመያዝ ነጥብ ተጋርተዋል።
ጋናዎች ግልፅ ፔናሊቲም ተከልክለዋል ። ካርሎስ ኬሮዥ የቀድሞው የፈርጊ ምክትል አንጋፋው አሰልጣኝ በቅርብ ግዜ የአቢዲ ፔሌ አንቶኒ የቦሃ ማይክል ኤሲየን ሱሊ ሙንታሪ ቶማስ ፓርቴ ሀገር ጋናን ይዘው በዓለም ዋንጫው ድንቅ አጀማመር አድርገዋል ።
ሃሪ ኬን በትናንትናው እለት አንድ ግልጽ የጎል እድል አግኝቶ በማይታመን ሁኔታ ሳይጠቀምበት ቀረ። ​ሃሪ ኬን በጨዋታው ላይ ጠፍቶ ነበር፤ በሚያስገርም ሁኔታ 19 ጊዜ ብቻ ኳስ ሲነካ የጋና ግብ ጠባቂ ቤንጃሚን አሳሬ ከሀሪ ኬን የበለጠ 31 ኳሶችን ነክቷል።
Black stars ከአሳማሆ ጂያን የደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ የድል መንፈስ ማስታወሻ ጋር በጀግንነት በህብረት እንደ ቡድን የሚዋደቅ ሁኖ አምሽቷል ። የጋናዎች አፍዝ አደንግዝ ጁጁ ካገኘ የማይስተው ኮኮቡ ሃሪ ኬንን ከጎሉ አፋፍ ጫፍ አደንዝዟል ። Via፦ ጋዜጠኛ ኤፍሬም የማነ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2