ከውጪ ሀገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ አራት ተጠርጣ ሪዎች ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

‎የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 መስቀል አደባባይ አካባቢ ሲሆን እስጢፋኖስ ተስፋዬ፣ ወንድሙ ደምሴ፣ ቦምሳ አብሳ እና ኢብራሂም አስፋው የተባሉት ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከመጣ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ላይ የስርቆት ወንጀል መፈጸማቸው ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ የግል ተበዳይን ሶፍት ግዛን ብለው በማዋከብና ትኩረቱን በማሳጣት ኪሱ ውስጥ የነበረውን ግምቱ 204 ሺ ብር የሚያወጣ Iphone17pro የተሰኘ ስማርት ሞባይል ስልክ ይዘውበት መሰወራቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል ።

‎በዕለቱ ከግል ተበዳይ የስልኩ መጥፋት ሪፖርት የደረሰው የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የክትትል ቡድን በማቋቋምና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጋር በቅንጅት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን ጠቁሟል።

በተደረገው ፈጣን የማፈላለግና የክትትል ስራም አራቱም ተጠርጣሪዎች ስልኩን እንደያዙ ከተኙበት ደምበል ዲሲ ከሚባል አካባቢ በዚያው ሌሊት በሰዓታት ልዩነት በቁጥጥር ስር በማዋል የግል ተበዳይ ከክ/ከተማው ዋና ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረ/ኮሚሽነር አድማሱ ኢፋ ንብረቱን የተረከቡ ሲሆን ፖሊስ ምርመራውንም እያሰፋ እንደሚገኝ ተገልጿል።

‎የሀገርም ውስጥም ሆነ የውጪ ሀገር ዜጎች በሠላም ወጥተው በሠላም እንዲገቡ ያለ ረፍት 24/7 የሚሰራ ቢሆንም ወንጀል ፈጻሚዎች አሳቻ ሰዓት እና ቦታ የሚጠቀሙ በመሆኑ በምሽት ለተለያዩ የግል ተግባራት ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ንብረቶቻቸውን በአግባቡ በመያዝ ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝም ወዲያው ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: