በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ማእቀፍ
ጠበቃና የህግ አማካሪ
ፋንታሁን ደለለው 0929101037
መግቢያ
#Ethiopia | ከትናንት ዛሬ እየተባባሰ የመጣው ከእለት እለት ስልክ በመደወል ቁጥሩ እየጨመረ የመጣው ለእቁብ ቁማር እና ለመሳሰሉት ገንዘቤን ተበላው አስመልስልኝ እባክህን እየተባለ የሚደወለው የስልክ ደውል አሁን ደግሞ በቅርብ የማውቃቻው ሰወች ይህን ያህል ገንዘብ ተበላው ያንተ መኖር ለእኛስ ካልሆነ ሙያህ ለሚቀርቡህ አይሆንም ወይ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ እና ማሳሰቢያ የዚህ ጹሁፍ መነሻዬ ሲሆን አጠቃላይ በእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባር ለተሳተፉ እና ለማህበረሰቡ ለግንዛቤ ይሆናል ከሚል መሠረታዊ ሀሳብ ይህንን እንድጽፍ አነሳስቶኛል።
1. እቁብ በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ
ማንኛውም ስራዎች በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ ተካተው ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ወይም ፖለቲካዊ ጥቅም ሊኖራቸው የሚገባ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። ይሁን እንጂ አሁን አሁን እቁብ ሎተሪ እየተባለ እያማለሉ በደካማ ስለንቦናቸው በመግባት ገንዘባቸውን እየዘረፉ ቢከሱ እንኳን ለማግኘት አስቸጋሪ
በሚሆነው ልክ ቅድሚያ ተዘጋጅተው በፍትህ ስረአት ውስጥ መተማመንን የሚያሳጡ የራስ አድር ባዮች በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ አለመተማመንን እያስነሱ ይገኛሉ። ይህንን ህገወጥ አካሄድ ለመግታት እና ለጥንቃቄ ያህል ይህ ጽሁፍ ለእናንተ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
2. እቁብ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ እንዴት ይታያል?
እቁብ አደራጆች በንግድ ስረአት ውስጥ ሆነው ተገቢውን የንግድ አሰራር እና ህግ ውስጥ በመግባት በአንዱ የንግድ
ማህበር ውስጥ በንግድ አዋጅ ቁጥር 1156/11 አንቀጽ 495
መሠረት የሚመቸውን መርጦ የንግድህግ ባለሙያ አማክሮ በንግድ መዝገብ አስመዝግቦ ተገቢውን ግብር እና ክፍያ ለመንግስትና ለሚመለከተው አካል እየከፈለ በህግ ሊተዳደር ይገባል እንጂ ሰውን አለአግባብ በማታለል ወይም በማማለል
በተለያየ ፕላትፎርም በአሳች ስም በመጠቀም ሰወች እንዲገቡ በማድረግ አላግባብ ገንዘባቸው እንዲዘረፍ እድል መክፈት፣ ማመቻቸት፣ መፈጸም ህገወጥ ተግባር ነው።
ይህ ህገወጥድርጊት ስለመፈጸሙ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰወች በተደጋጋሚ መደወል ከጀመሩ
ውለው ከርመዋል። ስለሆነም የንግድ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ
፣ያደረጉ፣ወይም ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ ያሉ በንግድ እና ሌሎች ህጎቻችን በሚደነግገው መሠረት በግል ንግድ ወይም በንግድ ማህበር በህጋዊ መንገድ ከመንቀሳቀስ በቀር ከዚህ ውጭ የሚያደርጉት ንግድ መሰል ድርጊት ህገወጥ ነው።
3. ተጠያቂነት
3.1 የወንጀል ተጠያቂነት
ይህንን ድርጊት ያለ ህግ እውቅና ሎቶሪ ወይም እቁብ በማለት
የሚያከናውኑ ሰወች በወንጀል በማታለል፣ በእምነት ማጉደል ወይም የህዝብን አደራ ገንዘብ ጋር በተያያዘ እንደ ወንጀል አፈጻጸሙ ክብደት የሚጠየቁበት ሲሆን ይህን በመረዳት ማህበረሰቡ ላይ ከሚያደርሱትም ጉዳት አንጻር ሊጠነቀቁ እና የሚመለከተው የፖሊስ እና የፍትህ አካላት ተገቢውን ክትትል እና እርምጃ ሊወስድ ያስፈልጋል።
3.2 የፍትሀብሄር ተጠያቂነት
ይህን ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ተጠያቂነት በወንጀል ብቻ ሳይሆን አላግባብ ህገወጥ
አካሄድ በተከተለ መንገድ ከአባላት ገንዘብ በመሰብሰብ በተለያየ መንገድ ለብዝበዛ በመታለል የተዳረጉ ሰወች እነዚህ አታላዮች አላግባብ ገንዘባቸውን የወሰዱባቸውን በፍተሀብሔር ህግ ቁጥር 2162 መሠረት የተወሰደባቸውን ገንዘብ ለማስመለስ መጠየቅ ይችላሉ።
4. አጠቃላይ የዚህ ጽሁፍ አጠቃላይ ምክር
እቁብ ወይም ሎተሪ በማለት ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው ይህንንም ሳያጣሩ እዚህ ተግባር ውስጥ በመሳተፍ ለገንዘብ ብዝበዛ የምትዳረጉ በመጀመሪያ አስፈላጊ ህጋዊ ነጋዴ ወይም የንግድ ማህበር ስለመሆናቸው፣የንግድ ፍቃድ፣ምዘገባና እና ሌሎች ህጋዊ ስረአት ያሟሉ ስለመሆናቸው በደንብ ሊያጣሩ ይገባል። በዚህ ስራ መሠማራት የምትፈልጉም ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና ስረአቶችን በሟማላት ብትፈጽሙ ለእናንተም ሆነ ለማህበረሰቡ አስተማማኝ ዋስትና ሲሆን የሚመለከተው የፍትህ አካላትም ከዚህ አንጻር አስፈላጊውን የህግ ግንዛቤ መስጠትና ቁጥጥር ሊያደርግ ያስፈልጋል።
ማጣቀሻ/Reference/
1. የኢፊድሪ ወንጀል ህግ
2. የፍትሀብሔር ህግ
Fantahun Delelew
https://www.facebook.com/share/1DTu52N8FU/
https://t.me/Fantahunlawyer
tiktok.com/@fantahun214
Source: GetuTemesgen









No comments yet.