የ18 ሚሊዮን ብር የፒካፕ ተሽከርካሪን አካል በትነው ለመሸጥ የሞከሩ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተማ ፖሊስ፣ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ በተደረገ የተቀናጀና ስኬታማ ክትትል፤ በአሽከርካሪነት የተቀጠረበትን የኮንስትራክሽን ድርጅት ንብረት የሰረቀ ግለሰብ ከስድስት ግብረ-አበሮቹ ጋር እጅ ከፍንጅ መያዙን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
አበራ መረሳ የተባለው ግለሰብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 (ልዩ ቦታው አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ) በሚገኝ አንድ የግል የኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ በአሽከርካሪነት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሲሆን፤ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ/ም የድርጅቱን ንብረት በመሰወር ወንጀሉን ፈጽሟል።
ግምቱ 18 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 48405 HILUX የሆነ ዘመናዊ የፒካፕ ተሽከርካሪ ነው።
ዋናው ተጠርጣሪ ከተባባሪዎቹ (ወንዶሠን አባተ፣ ሶይብ ሙኒር፣ ክንዱ ደጉ፣ ስንታየሁ ተመስገን፣ ብሩክ ግርማ እና ባህሉ ሲሳይ) ጋር በመሆን ተሽከርካሪውን ከአዲስ አበባ በመውሰድ በአዳማ ከተማ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ደብቀውታል።
እዚያም የተሽከርካሪውን አካል ሙሉ በሙሉ በመበታተን፣ ለአንድ ግለሰብ በ600 ሺህ ብር ለመሸጥ ተስማምተው የ110 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ (ቀብድ) ተቀብለው እንደነበር በምርመራ ታውቋል።
የአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ድርጊቱን በቅርብ ክትትል ሲያጣራ ቆይቶ፤ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከፌዴራልና ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር ባደረገው የጋራ ኦፕሬሽን ሰባቱንም ተጠርጣሪዎች ከተበታተነው የተሽከርካሪ አካል (ኤግዚቢት) ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የወንጀሉን መፈጸም ተከትሎ ለድርጅቶችና ለአሰሪዎች የሚከተለውን ማሳሰቢያ አስተላልፏል፦
“ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅት ሠራተኞችን አሽከርካሪዎችን በሚቀጥርበት ወቅት፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ የሠራተኞቻቸውን ማንነትና ታማኝነት የሚያረጋግጡ አስፈላጊ ህጋዊ ሰነዶችን በአግባቡ አሟልተው መያዝ ይኖርባቸዋል።”
Via የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ#ጉርሻ Page
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.