የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ ምን አሉ?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትና ሕዝብ ሰኔ 1 ቀን 2026 ዓ.ም ያካሄዱትን 7ኛውን አጠቃላይ ምርጫ በስኬት በማጠናቀቃቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ አድናቆት ገልጸዋል።

ሊቀመንበሩ ይህ የምርጫ ሂደት የኢትዮጵያውያን ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፣ ይህም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንደ መሠረት የሚወሰድ መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም አጠቃላይ ምርጫው በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ላሳየው የላቀ ሙያዊ ብቃትና ትጋት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

​ሊቀመንበሩ ባስተላለፉት መልዕክት ምርጫ ቦርድ ሰኔ 21 ቀን 2026 ዓ.ም ይፋ ባደረገው የምርጫ ውጤት መሠረት አብላጫ ወንበር በማሸነፍ አስደናቂ ድል ለተቀዳጁት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልፅግና ፓርቲ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው የእንኳን ደስ አላችሁ አጋርነታቸውን አብርክተዋል።

በመጨረሻም ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በአባል ሀገራት ዘንድ እውነተኛ ሰላማዊና ግልጽ የሆኑ የምርጫ ሂደቶች እንዲሰፍኑ በማድረግ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጠናከር የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በድጋሚ አረጋግጠዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: