አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ወንድማችን ዳንኤል ኤጄታ የሁለት ትናንሽ ልጆች አባት ነው። በኮቪድ-19 ምክንያት የደም መርጋት ችግር ተፈጥሮበት ደም ወደ እግሩ መድረስ ባለመቻሉ የደም ስሩ ተቀይሮ በሰው ሠራሽ (Artificial) የደም ሥር ተተክቶለታል።

እስካሁን ሰባት ጊዜ ቀዶ ሕክምና (Surgery) አድርጓል።

በአሁኑ ወቅት የተተከለው የደም ሥር እንደገና በመዘጋቱ በየቀኑ 13 ዓይነት መድኃኒቶችን እየወሰደ ይገኛል።

ሐኪሞች እግሩን ከማጣት ለመዳን በአስቸኳይ ወደ ውጭ አገር ሄዶ የስቴም ሴል (Stem Cell) ሕክምና እንዲሞክር መክረውታል። ይህ ሕክምና ካልተደረገለት ከጉልበቱ በታች ያለው እግሩ ሊቆረጥ እንደሚችል ተነግሮታል።

ዳንኤል ለዚህ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን ሕክምና የመሸፈን አቅም የለውም። ስለዚህ ወገን ለወገን ደራሽ በመሆን የወንድማችንን ሕይወት እንታደግ፤ ለልጆቹም እንዲተርፍ እንርዳው።

“ከጤና በላይ ሀብት የለም።”

ለመርዳት የምትፈልጉ ወገኖች በሚከተለው የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ድጋፋችሁን ማድረስ ትችላላችሁ።

የባንክ ሂሳብ ቁጥር: 1000272170677
ስም: Daniel Ejeta
ባንክ: Commercial Bank of Ethiopia (CBE)

የጎፈንድሚ ሊንክ ይጫኑ
https://gofund.me/bb0f0ac11

https://www.facebook.com/reel/1708490520494927/?app=fbl

እግዚአብሔር የሰጣችሁን ይባርክላችሁ፤
ሁላችንንም በጤና ይጠብቀን። 🙏🏽




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2