መርካቶ ፡ 3 ታማኝ ግብር ከፋዮች ተሸለሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የደረሰኝ አጠቃቀምን በማጠናከር፣ በህግ ተገዢነት እና በግብር ክፍያ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ 3 ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና ሽልማት ሰጥቷል።

በመርካቶ በተካሄደው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሚያገለግሉት አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን እንደገለፁት፣ የታክስ ህግን በአግባቡ በማክበር የሚሰሩ ግብር ከፋዮችን ለሌሎች አርአያ በሚሆን መልኩ ማበረታታትና እውቅና መስጠት የህግ ተገዢነትን ለማጠናከር ጠቃሚ ነው።

አቶ አብዱልቃድር አክለውም ሁሉም ግብር ከፋዮች ጤናማ የደረሰኝ አጠቃቀም ባህል በማዳበር እና የህግ ተገዢነት ደረጃቸውን በማሳደግ ለከተማዋ ልማት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ማጠናከር እንዳለባቸው ገልፀዋል።

የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በበኩላቸው፣ ቢሮው ከግብር ከፋዮች ጋር በቅርበት በመስራት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ተግቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ የዕለቱ የእውቅና ፕሮግራምም ታማኝ ግብር ከፋዮችን ለማበረታታት የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ መሀመድ በሰጡት አስተያየት፣ ገቢዎች ቢሮ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ በመስራት የግብር ከፋዮችን ችግር ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።

በመጨረሻም በደረሰኝ ግዢና ሽያጭ የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ 3 ታማኝ ግብር ከፋዮች የሰርተፊኬትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ቢሮው በቀጣይም በደረሰኝ ግብይት፣ በጥቆማ እና በህግ ተገዢነት የላቀ አፈፃፀም ለሚያሳዩ ዜጎችና ግብር ከፋዮች ተመሳሳይ የእውቅና መርሃ ግብሮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: