በታዋቂው ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ እና በሚዲያ ባለሙያው ግሩም ጫላ መካከል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሰላ የቃላት ምልልስ …

- Advertisement -
Sidebar AD
በታዋቂው ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ እና በሚዲያ ባለሙያው ግሩም ጫላ መካከል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሰላ የቃላት ምልልስ ተካሂዷል።
ይህ ውጥረት የጀመረው ግሩም ጫላ በፌስቡክ ገጹ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ለማድመቅ ያደረገውን ጥረት አድንቆ፣ ሆኖም በህንጻዎች ላይ የተተከሉት መብራቶች እየጠፉ ከተማዋ ወደ ጨለማ እየተመለሰች መሆኗን በመተቸት ባወጣው ጽሁፍ ነው። ግሩም በጽሁፉ ይህ ስራ ጊዜያዊ ሳይሆን ቋሚ እንዲሆን ክትትል ሊደረግበት እንደሚገባ አሳስቦ ነበር።
ይህንን የፌስቡክ ጽሁፍ ተከትሎ ጃዋር መሐመድ በኤክስ ገጹ ላይ የግሩምን ጽሁፍ በማያያዝ “ብልጭልጩ እየጨለመ ነው ይለናል ይህ ሞዴል ባለ ጊዜ” የሚል ፌዝ ያዘለ አስተያየት አስፍሯል።
ይህ የጃዋር አስተያየት ግሩምን ማስቆጣቱ አልቀረም። በግል የጽሁፍ መልዕክት  ግሩም ለጃዋር “አንተ ለመላው የኦሮሞ ማህበረሰብ ውርደት ነህ… በሁሉም መንፈስ የተሸጥክ ነህ” የሚል ከባድ ስድብ እንደላከለት፣ ጃዋር ያጋራው የስክሪን ሾት ማስረጃ ያሳያል።
ለዚህ የግሩም መልዕክት ጃዋር መሐመድ በይፋዊ የኤክስ ገጹ ላይ ጠንካራ ምላሽ ሰጥቷል። ጃዋር በመልዕክቱ “ግሩም ጫላ፣ የኦሮሞን አርሶ አደሮች የሚያፈናቅሉ፣ መሬታቸውን የሚሰርቁ እና ያገኙትን ገንዘብ በቅንጦት መኪናዎች ላይ የሚያባክኑና በዚህም የሚመጻደቁ እንዳንተ ያሉ ሌቦችን ማጋለጤ ‘የተሸጥክ’ የሚያስብለኝ ከሆነ፣ ያንን ስያሜ በክብር እለብሰዋለሁ” ሲል አስታውቋል።
ይህ በሁለቱ ግለሰቦች መካከል የተፈጠረው መካረር በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1