#Ethiopia | በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት አዝማሚያ መታየቱን ተከትሎ፣ በዚያ ሀገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲያከናውኑ ጥሪ አቀረበ።
ኢምባሲው ባወጣው መግለጫ በደቡብ አፍሪካ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝና ከሀገሪቱ መንግስት ጋር አስፈላጊ ግንኙነቶችን በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጿል።
የደቡብ አፍሪካ መንግስትም በስደተኞችና በውጭ ዜጎች ላይ የኃይል ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ በተለያዩ አካባቢዎች ተገቢውን የጸጥታ ጥበቃ እያደረገ መሆኑን ኢምባሲው ጠቁሟል።
በመግለጫው መሰረት ሁሉም ጉዳዮች በሕግ አግባብ እንደሚታዩ እና የሀገሪቱ መንግስት የጸጥታ ማስከበር ስራውን በቀጣይነት እንደሚያጠናክር ተገልጿል።
ሆኖም በስደተኞች ላይ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችና ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን በመጠቆም፣ በመላው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ንቁ በመሆን እና ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እንቅስቃሴያቸውን እንዲያከናውኑ አሳስቧል።
በተጨማሪም ዜጎች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች የመንግስት ተቋማትና የማህበረሰብ አደረጃጀቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲያደርጉ፣ መረጃዎችን እንዲለዋወጡ እና ለማንኛውም አደጋ ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።
– ኢትዮጵያ ኢምባሲ፣ ደቡብ አፍሪካ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.