በጋምቤላ ክልል አጭር ቀሚስ የሚለብሱ ሴቶች 3ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እየተቀጡ ነው ተባለ በጋምቤላ ክልል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በጋምቤላ ክልል አጭር ቀሚስ የሚለብሱ ሴቶች 3ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እየተቀጡ ነው ተባለ
 
በጋምቤላ ክልል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመቆጣጠርና የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ውሳኔዎች በመተግበር ላይ እንደሚገኙ  የክልሉ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን የአቦቦ ወረዳ ሴቶቸና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ውሳኔዎቹ ሊተላለፉ የቻሉት ልጆች ከወላጆች አቅም በላይ በመሆናቸው እና ትዕዛዝ ባለመስማታቸው ነው ሲል ፅ/ቤቱ አስታውቋል ።
 
ወላጆች መንግስት ይደግፈን ባሉት መሠረት ፕሮፖዛል ተቀርጾ እና ኮሚቴ ተዋቅሮ ፣ከፖሊስ ፣ከፍትህ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችሉ ውሳኔዎች ላይ እየተሰራ ይገኛል ። የአቦቦ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አዊሊ ኡጁሉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ሴቶች የሚለብሷቸው አጭር ቁመት ያላቸው ልብሶች የጥቃት ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።
 
ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲከታተሉና ልጆችም ከዚህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ የሚያስችሉ ጥብቅ መመሪያዎች መተላለፋቸውን ነግረውናል ።ይህንን ችግር ለመቅረፍ ለጥቃት አጋላጭ በሆነ መልኩ አጭር ልብሶችን ለብሰው በሚንቀሳቀሱ ሴቶች ላይ የ3ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መተላለፉን የነገሩን ኃላፊዋ መመሪያውን ተላልፈው በተገኙት ላይ የቅጣት እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ሲሉ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል ።
 
በመባ ወርቅነህ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: