ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከፌደራል ፖሊስ ኢንትለጀንስ ጋር በመቀናጀት በተሰራ ኦፕሬሽን በህገ ወጥ መንገድ የተከማቹ የሺሻ መጠቀሚያ ዕቃዎችና ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅና የሺሻ መጠቀሚያ እቃዎቹ ተከማችተው የተገኙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ወሰን አካባቢ ነው።
የተቀናጀ የምርመራ ኦፕሬሽኑ የተሰራው የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት መረጃ መሰረት በአካባቢው በሚገኙ ሆቴሎችና በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በቡድን በመሰባሰብ አደንዛዥ ዕፅ እና ሺሻ በሚጠቀሙና በሚያስጠቅሙ አካላት ላይ ነው።
በአካባቢው በተደጋጋሚ በተወሰደ እርምጃ ህገ ወጥ ተግባሩን የሚፈፅሙ ግለሰቦችን በጥናት በመለየት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ከየፌደራል ፖሊስና ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት በተሰራ ስራ የተገኘ ውጤት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡
በፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በተደረገ ፍተሻ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ከ900 ሊትር በላይ ቤንዚን በተጨማሪም በርካታ የሺሻ መጠቀሚያ ገመዶች፣ መዋስልሶች፣ ቡሬዎች፣ ሲጋራ እንዲሁም በርካታ ትራማዶል እና ማኮን መድሃኒቶችና የሲጋራ ማስታወቂያ ያለባቸው ቲሸርቶችን ተይዟል።
ህብረተሰቡ በየአካባቢው በድብቅ እየተበራከተ የመጣውን የአዋኪ ድርጊትን መንስኤዎችና ለወንጀል ድርጊት የሚያጋልጠውን የአደንዛዥ ዕፅ እና የሺሻ መጠቀሚያ ቦታዎችን ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ለማስወገድና ለትውልድ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር እያደረገ ያለው በጎ ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።



Source: Yeneta Tube








No comments yet.