”መልካም ወጣት የቆየው በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ድጋፍ ጭምር ነው” አገልጋይ ዮናታን

- Advertisement -
Sidebar AD

አክሊሉ

📌የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን
የ10ኛ ዓመት የምስረታ በዓሏን ልታከብር መሆኑ ተገለጸ

#Ethiopia | ​የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን የ10ኛ ዓመት የምስረታ በዓሏን እና የ“መልካም ወጣት ደማስቆ 2018” መክፈቻን አስመልክቶ በቤተ ክርስተመያኗ ዋና መጋቢ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የተመራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥታለች።

ቤተክርስቲያኗ በወንጌል አገልግሎት በማርሲል የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት እና በልዩ ልዩ ተግባራት የምታከብረው ይህ በዓል የ“መልካም ወጣት ደማስቆ” በተሰኝው የትምህርት ዝግጅትን ያካተተ ሲሆን ከሐምሌ 5 እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲከናወን ቀጠሮ ተይዞለታል።

”የቆምንበት አለት ” የ10 ኛ ዓመት የምስጋና ዝግጅቱም ከሰኔ 21 እስከ 28 ቀን በቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን ሁሉ እንዲገኝ ጥሪ ተላልፏል።

​ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ200 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ ስኬታማ መሪዎችንና ባለሙያዎችን አፈራ የተባለው ይህ ፕሮጀክት፣ዘንድሮ በስምንት ዙሮች እስከ 40 ሺህ ወጣቶችን ለመቀበል አቅዷል።

አገልጋይ ዮናታን በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጭምር ድጋፍ ይደረግለታል ያሉት ”የመልካም ወጣት” ፕሮጀክት የአቅመ ደካማ ወላጆችንና የወጣቶችን የኑሮ ጫና ታሳቢ በማድረግ ቀደም ሲል 1,500 ብር የነበረው የአገልግሎት ክፍያ ከራዕዩ ጎን በቆሙ ወገኖች ድጋፍ ወደ 700 ብር ዝቅ መደረጉን ገልጸዋል።

ይህ ክፍያ ወጣቶቹ በሐዋሳ ለሚኖራቸው የአንድ ሳምንት ቆይታ ሙሉ የምግብና የመኝታ ወጪን የሚሸፍን ሲሆን የአገልግሎት ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋት በወላይታ ግንባታ እያከናወነ መሆኑን ሰምተናል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: