የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤኤምኤን) ዜና አንባቢው ሳህለገብርኤል ይትባረክ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) ዜና አንባቢ ምክትል ኢንስፔክተር ሳህለገብርኤል ይትባረክ ዛሬ ማለዳ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ።

ትናንት በሚዲያው ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕለታዊ ዜናውን አንብቦ የሄደው ጋዜጠኛው ዛሬ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ መላውን የሥራ ባልደረቦቹን ወዳጅ ዘመዶቹንና ተመልካቹን በከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ውስጥ ጥሏል።

​በሁሉ ዘንድ በትሕትናውና በሥራ ወዳድነቱ የሚታወቀው የምክትል ኢንስፔክተር ሳህለገብርኤል ይትባረክ ድንገተኛ መርዶ፣ የሰውን ልጅ ሕይወት አጭርነትና ቅጽበታዊነት መሆኑን ያሳየና እጅግ ልብ የሚሰብር ሆኗል።

ይህንን መራራና አስደንጋጭ ዜና ተከትሎም፣ ለታዋቂው የዜና አንባቢ ቤተሰቦች፣ ለቅርብ ወዳጆቹና ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ ባልደረቦች በሙሉ ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።

ነፍስ ይማር 🕯



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2