8ኛው አግሮ ፉድ ፕላስትፕሪንትፓክ ኢትዮጵያና 2ኛው የኢትዮጵያ ቡናና ምግብ ንግድ ትርዒት

- Advertisement -
Sidebar AD

ተከፈተ

#Ethiopia | ​የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዕድገትና ሰፊ እምቅ አቅም የሚያሳየው 8ኛው “አግሮፉድ እና ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጵያ” ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር በይፋ ተከፍቷል። ከሰኔ 18 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ ከ18 አገራት የተውጣቱ 153 ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን፣ በኹነቱን 2ኛው የኢትዮጵያ የምግብ ንግድ ትርዒት እና የኢትዮፒካ የቡና ንግድ ትርዒትም ጎን ለጎን እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ መድረክ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ስኬታማ ዓለም አቀፋዊ የኢንዱስትሪ ትስስር የሚፈጥር መሆኑ በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገልጿል።

​ኢትዮጵያ በምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያ እንዲሁም በማሸጊያ ቴክኖሎጂ ላይ በየዓመቱ ከ64 ሚሊዮን እስከ 171 ሚሊዮን ዩሮ የሚደርስ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ወደ ሀገር ቤት ከሚያስገቡ አገራት አንዷ መሆን ችላለች ተብሏል።

በተመሳሳይ መልኩ የሀገሪቱ የፕላስቲክ ፍጆታ በየዓመቱ በአማካይ የ11.5% የተረጋጋ ዕድገት በማሳየት እ.ኤ.አ በ2007 ከነበረበት 44 ኪሎ ቶን በ2024 ወደ 281 ኪሎ ቶን ከፍ ብሏል። ይህ ዓይነቱ ፈጣን የፍጆታ ዕድገትም ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሁለተኛዋ ታላቅ የፕላስቲክ ጥሬ ዕቃ አስመጪ አገር እንድትሆን አድርጓታል።

​በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ እንደ ብራዚል፣ ቻይና፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶችና እንግሊዝ ከመሳሰሉ አገራት የመጡ ኩባንያዎች መሳተፋቸው ስፍራው ላይ ተገኝተን ተመልክተናል።

በጀርመኑ ፌርትሬድ (fairtrade Messe) እና በሀገር ውስጥ አጋሩ ፕራና ኢቨንትስ ትብብር የተዘጋጀው ይህ ኤግዚቢሽን በሺህዎች የሚቆጠሩ የዘርፉን ባለሙያዎች ከአገር ውስጥና ከመላው ዓለም በማገናኘት በምስራቅ አፍሪካ አግሮፉድ፣ ፕላስቲክና የቡና ንግድ ላይ ፈሰስ ላደረገ ማንኛውም አካል የማይታለፍ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድል ይዞ ቀርቧል ተብሏል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1