#Ethiopia | ቴክኖ ኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚያዘጋጀውን “ሀገርን በምስልና በታሪክ የማስጎብኘት” ፕሮግራም ዘንድሮም በአዲሱ TECNO CAMON 50 Pro የተነሱ ፎቶዎችን እና ከእነሱ ጋር የተያያዙ ታሪኮችን በማቅረብ ለ10 ቀናት የሚቆይ ኤግዚቢሽን ሊያካሂድ ነው።
ኤግዚቢሽኑ ከሰኔ 27 እስከ ሐምሌ 4 ድረስ በአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና የሕፃናትና ወጣቶች ቲያትር ኮምፕሌክስ በትብብር የሚካሄድ ሲሆን፣ ቦታውም ከፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ በሚገኘው የሕፃናትና ወጣቶች ቲያትር ይሆናል።
የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ሰኔ 27 ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት የሚካሄድ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ውብ መልክዓ ምድሮች፣ ባህሎችና ታሪኮች በፎቶ ማየት ብቻ ሳይሆን፣ የTECNO CAMON 50 Pro ስልክ ተሸላሚ የመሆን እድልም ያገኛሉ።
ቴክኖ ኢትዮጵያ ለሁሉም የሀገር ወዳዶች ከቤተሰብና ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በዝግጅቱ እንዲሳተፉ፣ ሀገራቸውን እንዲያዩ፣ እንዲዝናኑ እና ሽልማት እንዲያሸንፉ ጥሪ አቅርቧል።
#Ethiopia #AddisAbeba #TECNO #TECNOCAMON50Pro #PhotoExhibition #Tourism #Photography #TechNews #Events #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.