#Ethiopia | ሚኒስትሯ በይፋዊ የ’ኤክስ’ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት አጭር መልዕክት፣ እርሳቸው ቀደም ሲል ከተመረቁበት አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የበኩር ልጃቸው ተምራ በማጠናቀቋ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት ገልጸዋል።
እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ ልጃቸው ኸይሪያ አወል ዋግሪስ ትምህርቷን የተከታተለችው በ’ሎጀስቲክስ እና ሰፕላይ ማኔጅመንት’ የትምህርት ዘርፍ ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ ያስመረቀ ሲሆን፣ እንደ ዘሐበሻ ዘገባ የሚኒስትሯ የደስታ መግለጫም የዚሁ ትልቅ አገራዊ የምረቃ ስነ-ስርዓት አካል ነው።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.