#Ethiopia | በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በቀዳሚነት በተካሄደው ውድድር ቤተልሔም ዳንኤል በ80 ኪ.ሜ የሴቶች ኤሊት ውድድር አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች።
እንዲሁም ፍሊሞን ዘርአ ብሩክ በ140 ኪ.ሜ የወንዶች ኤሊት ውድድር ቀዳሚ ሆኗል።
ሁለቱም አሸናፊዎች በካናዳ ሞንትሪያል ለሚካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ።
ውድድሩ በካናዳ ሞንትሪያል ለሚካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና (ሀCI) ላይ ሀገራችንን ወክለው የሚሳተፉ ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ የተደረገ ዋና መድረክ እንደሆነ ተነግሯል።
ባለፉት ዓመታት በተደረጉ መሰል ብሔራዊ ሻምፒዮናዎች ላይ የተገኙ ውጤቶች ስፖርተኞቻችን በጀርመን እና በቻይና ፕሮፌሽናል ክለቦችን እንዲቀላቀሉ ዕድል የፈጠሩ ነበር ተብሏል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#የኢትዮጵያብስክሌትሻምፒዮና
#ካናዳሞንትሪያል
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication



Source: GetuTemesgen









No comments yet.