ዩስራ ሆም በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን የአሽሊ ፈርኒቸር ቅርንጫፍ ከፈተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ባለፈው ጥር ወር ላይ የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በብስራተ ገብርኤል አካባቢ የከፈተው ዩስራ ሆምስ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በዛሬው እለት በጉርድ ሾላ ከፍቷል።

በአሜሪካ ለ80 ዓመታት አለም አቀፍ ብራንድ ሆኖ የዘለቀው አሽሊ ፈርኒቸር ለዩስራ ሆም በሰጠው የብቸኛ ወኪልነትና አቅራቢነት ፍቃድ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለተኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ የዩስራ ሆም መሥራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዩስራ ኑርሁሴን ረጃ፣ እንዲሁም የአሽሊ ፈርኒቸር የሥራ መሪዎች በተገኙበት ተመርቋል።

በዓለም የፈርኒቸር ኢንዱስትሪ ስመጥር የሆነው የአሜሪካው አሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በይፋ መግባቱ፣ የሀገሪቱን የግንባታና የእንግዳ ተቀባይነት (Hospitality) ዘርፍ ተስፋ ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑም ተገልጿል።

የዩስራ ሆም መሥራች ወይዘሮ ዩስራ ኑር ሁሴን ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ፣ የታሪክ እና የባህል ፀጋዎች በመጠቀም አዳጊ የቱሪዝም ተስፋ ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቀደሚ እየሆነች ትገኛለች ብለዋል።

በአሽሊ ፈርኒቸር የአፍሪካ እና የእንግሊዝ ምክትል ፕሬዚዳንት ማርክ ማራስ በምረቃ መርሀ ግብሩ ዕለት በሰጡት መግለጫ ዩስራ ሆም ከአሽሊ ፈርኒቸር የሚጠበቀውን መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱን ተናግረዋል።

በዚህም የወኪልነት እና የአቅራቢነት ማረጋገጫ መስጠቱን ተናግረዋል።

አሽሊ ፈርኒቸር በፍሬንቻይዝ ለዩስራ ሆም ምርቶቹን በማቅረቡ ኩራት ይሰማዋል ሲሉም ሚስተር ማርክ ተናግረዋል።

የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ዕድገቷ የሚታይ እና እኛ ልንፈጥር ላሰብነው ገበያ የምትመች ናት ሲሉም ለከተማዋ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

የአሽሊ ፈርኒቸር ወደ ኢትዮጵያ መግባት ከሀገሪቱ የቱሪዝም እና የግንባታ ዘርፍ ጋር ያለውን ግንኙነት ያጠናክረዋል ሲሉ የዩስራ ሆም የሥራ መሪዎች ተናግረዋል።

በተጨማሪም ቀደም ሲል ሆቴሎች እና አልሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገር በመጓዝ ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል ተብሏል።

የ80 ዓመታት ልምድ ያለው የአሽሊ ፈርኒቸር የንድፍ እና የጥራት ደረጃዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው፣ ለሀገር ውስጥ የፈርኒቸር ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር እንደሚፈጥርም ተነግሯል።

በአጠቃላይ የአሽሊ ፈርኒቸር እና የኢትዮጵያ ግንኙነት መጀመር፣ የሀገሪቱን የንግድ ኢንቨስትመንት ከማሳደጉም በላይ የቱሪዝም ዘርፉ የሚፈልገውን ዘመናዊ ገፅታ ያላብሳል ተብሏል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#ዩስራሆምጉርድሾላ
#አሽሊፈርኒቸር #ፈርኒቸር
#አሜሪካኤምባሲ #ኢርቪንማሲንጋ
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgenmediacommunication






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: