ቀብር

- Advertisement -
Sidebar AD

‎የአቶ ሀይሉ ሀብተሚካኤል አጭር የሕይወት ታሪክ

‎#Ethiopia | ​​አቶ ሀይሉ ሀብተሚካኤል ከአባታቸው ከአቶ ሀብተሚካኤል አስናቀ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አበበች ገ/ጻዲቅ በሰሜን ሸዋ፣ በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ፣ ልዩ ስሙ ደግማት በተባለ ሥፍራ መስከረም 19 ቀን 1940 ዓ.ም ተወለዱ።

ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

‎​ወደ ሥራ ዓለም በመግባትም በ1964 ዓ.ም በኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ፋብሪካ (ፔፕሲ ) ተቀጥረው፣ በታማኝነትና በትጋት እስከ ጡረታ ዘመናቸው ድረስ አገልግለዋል።

‎​በትዳር ሕይወታቸው ከወ/ሮ አመለወርቅ ተክሉ ጋር ትዳር መስርተው 5 ወንድና 2 ሴት (በአጠቃላይ 7) ልጆችን አፍርተዋል፤ እንዲሁም 13 የልጅ ልጆችን ለማየት በቅተዋል።

‎​አቶ ሀይሉ በእርጅናና በሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው፣ በተወለዱ በ78 ዓመታቸው ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

‎የክቡር አባታችን የ ሥነ ሥርዓት ነገ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: