በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተፈረደባት ለይላ ኑርሰቦ ከ13 እስር በኋላ ኢትዮጵያ ገባች

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በሳውዲ አረቢያ ለረጅም ዓመታት በእስር ላይ የቆየችው እና የሞት ፍርድ ተላልፎባት የነበረው ኢትዮጵያዊቷ ወ/ሪት ለይላ ኑርሰቦ ረዲ፣ በተደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እና እርቅ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳለች።

​ወ/ሪት ለይላ ኑርሰቦ በሳውዲ አረቢያ ለ13 ዓመታት በእስር ላይ የቆየች ሲሆን፣ በወቅቱ በነበረው የህግ ሂደት የሞት ፍርድ ተፈርዶባት እንደነበር ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግስት እና በሳውዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሲሰሩ ቆይተዋል።

​ለዚህ ውጤት መሳካት በኢትዮጵያ ኤምባሲ የተደረገው ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት፣ የተደረገው የእርቅ ሂደት እና ለተጎጂ ቤተሰቦች የተከፈለው የካሳ ክፍያ ወሳኝ ሚና እንደነበራቸው ተገልጿል።

​የወ/ሪት ለይላ መፈታት እና ወደ አገሯ መመለስ በብዙዎች ዘንድ አዎንታዊ ምላሽን አግኝቷል። በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኮሚቴ አባላት፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ለሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም ጉዳዩን በቅርበት ለተከታተሉ መላው ኢትዮጵያውያን ምስጋና ቀርቧል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1