በጎንደር ከተማ በመንግሥቱ ወርቁ ስም ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ ተሰይሞ ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​በጎንደር ከተማ በዞብል ክፍለ ከተማ በተለምዶ ፖሊስ ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ዘመናዊ የእግር ኳስ ማዘውተሪያ ሜዳ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በይፋ ተመርቋል።

‎የወጣቶችን ስፖርታዊ ተሰጥኦ ለማሳደግና ጤናማ ማኅበረሰብን ለመገንባት ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ብርሃን የሆነውን የታላቁን ጀግና ስም በመውሰድ «የመንግሥቱ ወርቁ መታሰቢያ እግር ኳስ ሜዳ» ተብሎ ተሰይሟል።

‎​ኢንስትራክተር መንግሥቱ ወርቁ፣ በምዕራብ ጎንደር ቋራ ተወልደው ከመቃብር በላይ የሚኖሩ አኩሪ ሥራዎችን ለሀገራቸው ያበረከቱ የኢትዮጵያ እንቁ ናቸው። የመጀመሪያው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ኢንስትራክተር የነበሩት ይህ ጀግና፣ ለብሔራዊ ቡድኑ 61 ጎሎችን በማስቆጠር የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ መሆናቸውን የታሪክ ማኅተም አሳርፈዋል።

‎ኢትዮጵያ የ3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ በታላቅ ድል ስታነሳ ቡድኑን በብቃት የመሩትና የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች የነበሩት እኚሁ የቋራ አንበሳ፣ ለ23 ዓመታት በታማኝነት ላገለገሉት ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በነበራቸው ክብር ሳቢያ ታሪካዊት የ8 ቁጥር ማሊያቸው በክለቡ ቤት ተሰቅላ ትገኛለች። ከተጫዋችነት ባሻገር ስድስት ያህል ክለቦችንና ብሔራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት የመሩት የታሪኩ ባለቤት፣ ዛሬ በትውልድ ቀያቸው በክብር እንዲታደሱ ተደርጓል።

‎​በምረቃ መድረክ ላይ የጀግናው ልጅ አቶ አምባቸው መንግሥቱ ወርቁ በአካል ተገኝተው በአባታቸው ስም ሜዳው በመሰየሙ የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ የገለጹ ሲሆን፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቦርድ ተወካይ አቶ ሰለሞን መርጋሳ እና ደራሲ ዶክተር ሰለሞን በርሄም ተገኝተዋል።

ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: