አሜሪካ ተማሪዎቿን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነቡ ልታስደርግ ነው።የቴክሳስ ግዛት ተማሪዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንዲያነቡ ሊያ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አሜሪካ ተማሪዎቿን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያነቡ ልታስደርግ ነው።
የቴክሳስ ግዛት ተማሪዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንዲያነቡ ሊያስገድድ መሆኑ ተዘግቧል።
በአሜሪካ የቴክሳስ ግዛት የትምህርት ምክር ቤት በግዛቲቱ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንዲያነቡ የሚያስገድድ አዲስ የንባብ ዕቅድ በ9 የድጋፍ በ5 የተቃውሞ ድምፅ አጽድቋል።
ከሦስት ዓመት በኋላ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ እቅድ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ብቻ ሳይሆን የቻርልስ ዲከንስ “Great Expectations” እና የዊሊያም ሼክስፒር “The Tragedy of Julius Caesar” የመሳሰሉ ታዋቂ የእንግሊዝ ሥነ-ጽሑፍ ሥራዎችንም ያካትታል ነው የተባለው።
ውሳኔው በአሜሪካ ውስጥ በሃይማኖትና በመንግሥት መለያየት ላይ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል።
ደጋፊዎቹ የአይሁድ-ክርስትና እሴቶችና ባህሎች በአሜሪካ ታሪክና ምሥረታ ውስጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው በመግለጽ ተማሪዎች ሊያውቋቸው ይገባል ይላሉ።
የቴክሳስ የትምህርት ቦርድ አባል ብራንደን ሆል “መጽሐፍ ቅዱስን ከ60 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤቶች እየመለስን ነው” ብለዋል።
በሌላ በኩል ተቃዋሚዎች እቅዱ የሃይማኖት ነፃነትን የሚጎዳ፣ ክርስትናን ከሌሎች ሃይማኖቶች በላይ የሚያቆም እና የአሜሪካን ባህላዊ ብዝሃነት የሚያቀል መሆኑን ይናገራሉ።
የ“Freedom Network” ዋና ዳይሬክተር ፌሊሺያ ማርቲን እቅዱ ሌሎች ሃይማኖቶችን፣ የቀደምት አሜሪካውያንን እና የተለያዩ ማህበረሰቦችን አስተዋፅኦ ችላ እንደሚል ተችታለች።
ተማሪዎች ከአዲስ ኪዳን ውስጥ ስለ ኢየሱስ የሚናገሩ ክፍሎችን እና “የጠፋው ልጅ” የሚባለውን ምሳሌ እንዲማሩ በእቅዱ ተካትቷል።
እንዲሁም የቴክሳስ መምህራን ማህበር እቅዱ በጣም ሰፊ መሆኑን እና መምህራን ለተማሪዎቻቸው ተገቢ የሆኑ መጽሐፍትን የመምረጥ ነፃነታቸውን ሊያሳንስ እንደሚችል ገልጿል።
ይህ ውሳኔ በቴክሳስ ውስጥ ክርስቲያናዊ እሴቶችን በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ለማጠናከር ከተወሰዱ ተከታታይ እርምጃዎች አንዱ ሲሆን፤ ባለፈው ዓመትም በትምህርት ክፍሎች ውስጥ የአሥርቱ ትዕዛዛት እንዲሰቀሉ የሚያስገድድ ሕግ ተላልፎ ነበር፤ ይህም በፌዴራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ድጋፍ አግኝቷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔውን በመደገፍ በአሜሪካ ውስጥ የሃይማኖት እሴቶችን ለማጠናከር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልጸው፣ “ሃይማኖት ከቀድሞው የበለጠ ጠንካራ ሆኖ ወደ አገራችን ተመልሷል” ብለዋል።
በአጠቃላይ ውሳኔው በአሜሪካ የትምህርት፣ የሃይማኖት ነፃነት እና የመንግሥት-ሃይማኖት ግንኙነት ላይ ሰፊ ውይይት እንዲቀጥል አድርጓል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: