ዶላር ጉዱ ፈላ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ቻይና በየዓመቱ በሻንጋይ በሚካሄደው የሉጂያዙይ ፎረም ላይ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ላይ ያለውን ፍጹም የበላይነት ለመገዳደር የሚያስችላትን አዲስ ስትራቴጂ ይፋ አድርጋለች።

ቤጂንግ ያቀረበቻቸው አዳዲስ እርምጃዎች (RMB) የውጭ ፋይናንስን ማሳደግ ለውጭ ሀገራት ማዕከላዊ ባንኮች አዳዲስ የፋይናንስ አቅርቦቶችን መፍጠር እና የድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጦችን ማስፋፋት ላይ ያተኮሩ ናቸው።

ይህ ሂደት ዶላርን በአንድ ጀምበር ሙሉ በሙሉ ለመተካት ሳይሆን የቻይናን እና የሌሎች ሀገራትን በዶላር መዋቅር ላይ ያለውን ጥገኝነት ደረጃ በደረጃ ለመቀነስ ታስቦ በተግባር እየተገነባ ያለ አማራጭ የፋይናንስ ልማት ነው።

​ይህ የቤጂንግ እንቅስቃሴ ከገንዘብ ነክ ጉዳይ ይልቅ ትልቅ የጂኦፖለቲካ ፍልሚያ ሲሆን አሜሪካ ላለፉት ሰማንያ ዓመታት በዶላር ኃይል በመጠቀም ስትጠቀምባቸው የነበሩትን እንደ ማዕቀብ መጣልና የዓለምን የካፒታል ፍሰት መቆጣጠር ያሉ የፖለቲካ ተፅዕኖዎችን ለመቀየር ያለመ ነው።

ቻይና ይህንን የአሜሪካን የአንድ ወገን የፋይናንስ የበላይነት ለመገዳደርና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አዲስ አማራጭ መድረክ ለመፍጠር በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ ምቹ ጊዜ ላይ ትገኛለች።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1